Fana: At a Speed of Life!

በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች የሚውል የ45 ሚሊየን ብር የምግብ ፍጆታ ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 22 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አዋሽ ባንክ በኦሮሚያ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች የሚውል የ45 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የምግብ ፍጆታ ድጋፍ አደረገ፡፡

ድጋፋ ድርቅ በተከሰተባቸው ቦረና፣ ጉጂና ባሌ አካባቢዎች ለሚገኙ ዜጎች ተደራሽ ይሆናል ተብሏል።

የአዋሽ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አምባሳደር ዲባባ አብደታ÷ ባንኩ እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን መደገፍ ማህበራዊ ሀላፊነቱ መሆኑን ገልጸዋል።

የተደረገው ድጋፍ በክልሉ በድርቅ ለተጎዱ በመድረስ ችግሩን ለመቅረፍ የሚደረገውን ጥረት ያግዛል ብለዋል።

ባንኩ በልማት፣ የሰብዓዊ እርዳታ እና የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ላይ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ አጠናክሮ ይቀጥላልም ነው ያሉት።

ድጋፋን የተረከቡት የኦሮሚያ ክልል የአደጋ መከላከልና ዝግጁነት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ሙስጠፋ ከድር በድርቁ ምክንያት 3 ነጥብ2 ሚሊየን ሰዎች ለእርዳታ መጋለጣቸውን ገልጸዋል።

በክልሉ የተከሰተው ድርቅ የፈጠረውን ችግር ለመፍታት መንግስት ጥረት እያደረገ መሆኑን ያነሱት ኮሚሽነሩ ከችግሩ ስፋት አንፃር በመንግስት የሚደረጉ ድጋፎች በቂ ባለመሆናቸው ተቋማት ድጋፍ ማድረግ ይጠብቅባቸዋል ብለዋል።

በክልሉ በተከሰተው ድርቅ የተጎዱ ዜጎችን ለመደገፍ ባንኩ ላደረገው ድጋፍም ኮሚሽነሩ ምስጋና አቅርበዋል።

በቅድስት አባተ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.