Fana: At a Speed of Life!

የኦነግ የቀድሞ ሊቀመንበር ገላሣ ዲልቦ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የቀድሞ ሊቀመንበር ገላሣ ዲልቦ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በገላሣ ዲልቦ እረፍት የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀዋል።

አቶ ሽመልስ በሀዘን መግለጫቸው “ኦሮሚያ ጠንካራ ሰው አጥታለች” ብለዋል።

“ገላሣ ዲልቦ የኦሮሞ ነፃነት ታጋይ ነበሩ” ያሉት አቶ ሽመልስ፥ ሙሉ ህይወታቸውን ለኦሮሞ ህዝብ የገበሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በሀዘን መግለጫቸው ለኦሮሞ ህዝብ በሙሉ ብርታትን እና መፅናናትን እመኛለሁ ብለዋል።

አንጋፋው ፖለቲከኛ አቶ ገላሳ ዲልቦ አግላይ ስርዓትን በመታገል በሀገሪቱ ፍትሃዊነት እንዲነግስ ታግለዋል፡፡

አቶ ገላሳ ዲልቦ በአገሪቱ የነበረውን የአገዛዝ ስርዓት በመቃዎም ከኦሮሞ ነፃነት ግንባር ጋር ለ40 ዓመታት ትግል አድርገዋል፡፡

በተለይም በኦሮሞ የፖለቲካ ታሪክ ሰፊ ተሳትፎ የነበራቸው ሲሆን፥ በ2014 ዓ.ም በተካሄደው ምርጫ የምሥራቅ ሐረርጌን ህዝብ ወክለው በመወዳደር በማሸነፍ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ሆነው በማገልገል ላይ ነበሩ።

በተለያዩ ሚዲያዎች ቀርበው ባደረጉት ቃለ ምልልስም በኢትዮጵያ ሀገረ መንግስት ታሪክ፥ “ጨቋኝ ስርዓት እንጂ ጨቋኝ ብሄር የለም” በማለት የገዥና ተገዥ የብሄር ትርክትን ከሚቃወሙ ፖለቲከኞች አንዱ መሆናቸውን አሳይተዋል፡፡

የአቶ ገለሳ ድልቦ የቀብር ስነ-ስርዓት የፊታችን ቅዳሜ መጋቢት 24 ቀን 2014 ዓ.ም በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ይፈፀማል።

 

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.