Fana: At a Speed of Life!

ከሳዑዲ አረቢያ በሁለተኛ ዙር 438 ዜጎች ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሳዑዲ አረቢያ በሁለተኛ ዙር 438 ዜጎች ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡

ዛሬ ጠዋት የመጀመሪያ ዙር ተመላሾች የገቡ ሲሆን÷ ከሰዓት በኃላ ደግሞ በሁለተኛው ዙር በረራ 438 ዜጎች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ተመላሾቹ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንስላ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄነራል የስራ ኃላፊዎች አምባሳደር ሲራጅ ረሺድ፣ አቶ መስፍን ገ/ማርያም፣ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የስራና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ አቶ አራርሳ ቢቂላ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሴቶች፣ ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሀና የሺንጉስና ሌሎች የስራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በሳዑዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ብሔራዊ አስፈፃሚ ኮሚቴ በማዋቀር የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ሲከናወኑ መቆየቱ ይታወሳል።

 

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.