Fana: At a Speed of Life!

የፌደራል ፖሊስ ኢትዮጵያን የሚመስል መዋቅራዊ አደረጃጀትና ስያሜ ማዘጋጀቱን ገለፀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ፖሊስ ኢትዮጵያን የሚመስል መዋቅራዊ አደረጃጀትና ስያሜ አዘጋጅቶ በመካከለኛ ደረጃ ለተመደቡ አመራሮች የመሪነት ስልጠና መስጠቱን አስታወቀ፡፡
በፌደራል ፖሊስ በዋና ክፍል የተመደቡት መካከለኛ አመራሮች በተመደቡበት የሥራ መስክ በታማኝነትና በቅንነት ህዝብን እንዲያገለግሉ ቃለ-መሃላ በመፈፀም አዲሱ ተቋማዊ መዋቅር፣ አደረጃጀትና የትራንስፎርሜሽን መሪ ሚናን በሚገባ ተረድተው የተቋሙን የ10 ዓመት ዕቅድ ለማስፈፀም የሚያስችል አቅም እንዲፈጥሩ በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ወስደዋልም ተብሏል፡፡
መኮንኖቹ በሁሉም የተቋሙ አደረጃጀቶች ሥር የዋና ክፍል ኃላፊዎች ሆነው ለኃላፊነት ሲመደቡ በአዲሱ መዋቅር የሰው ኃይል አደረጃጀትን መሰረት አድርጎ የምልመላው መስፈርት የማዕረግ ቀደምትነትን፣ የሥራ ልምድን፣ የትምህርት ደረጃንና ኢትዮጵያን የሚመስል የፖሊስ ተቋም ለመገንባት የሴቶች ተዋፅኦና ኅብረ-ብሔራዊነትን ግምት ውስጥ ያስገባ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል፥ የተቋሙን የ10 ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድና በፀጥታ ዘርፍ የለውጥ ፅንሰ ሃሳብ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በፖሊስ አሰራር ጥሩ ልምድ ያላቸው አገሮችን ተሞክሮን እንዴት መጠቀም እንደሚቻል አብራርተዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.