Fana: At a Speed of Life!

የኢንቨስትመንት እና የኢንዱስትሪ ፓርኮች የማስተዋወቂያ መድረክ በህንድ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽንና የህንድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በጋራ ያዘጋጁት የኢንቨስትመንት እና የኢንዱስትሪ ፓርኮች የማስተዋወቂያ መድረክ በህንድ ሙምባይ ከተማ መጀመሩ ተገለጸ።

በህንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ትዝታ ሙሉጌታ እና ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዳንኤል ተሬሳ በኢትዮጵያ ስላሉ የኢንቨስትመንት ዕድሎች እና አማራጮች ለህንድ ባለሀብቶች ገለፃ አድርገዋል፡፡

በተጨማሪም ኮሚሽኑ ከህንዱ የኢኮኖሚ እና የንግድ ተቋም ጋር የሁለቱን ሀገራት የኢንቨስትመንት ግንኙነትን ማጠናከር አላማው ያደረገ የመግባቢያ ሰነድ መፈረሙን ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

መድረኩ ለ15 ቀናት እንደሚቆይ ተገልጿል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.