Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ታንዛኒያ በወታደራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመሥራት ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 19 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና ታንዛኒያ በወታደራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ መሥራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡
 
ስምምነቱን በኢፌዴሪ መከላከያ የሜካናይዝድ ማስተባበሪያ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል አለምእሸት ደግፌና የታንዛኒያ መከላከያ ሠራዊት ኤታማዦር ሹም ሌተናል ጀኔራል ማሥዪ ሚክንጉሌ ተፈራርመውታል።
 
ስምምነቱ ኢትዮጵያና ታንዛኒያ በወታደራዊው ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው ሌተናል ጀኔራል አለምእሸት ደግፌ መናገራቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ሌተናል ጄ ማስዪ ሚክንጉሌ በበኩላቸው÷ የተደረገው የሁለትዮሽ ስምምነት ለሀገራቱም ሆነ ለቀጠናው ሰላምና ደህንነት መጎልበት የራሱ ጠቀሜታ እንደሚኖረው አመላክተው ለልዑካን ቡድኑ ለተደረገው አቀባበልም ምስጋና አቅርበዋል።
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.