ደመናን የማበልፀግ ቴክኖሎጂ የበልግ ዝናብ አጋጣሚን በመጠቀም በድርቅ ተጎድተው በቆዩት የቦረናና ኮንሶ አካባቢ የሙከራ ትግበራ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ደመናን የማበልፀግ ቴክኖሎጂ የበልግ ዝናብ አጋጣሚን በመጠቀም በድርቅ ተጎድተው በቆዩት የቦረናና ኮንሶ አካባቢ ሁለተኛ ዙር የሙከራ ትግበራ እየተካሄደ ነው።
ካለፈው ረቡዕ ጀምሮ በአካባቢዎቹ ደመናን የማበልጸግ ስራ ተከናውኗል።
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ከብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፥ ደመና የማበልፀግ ስራውን ተከተሎም በሰሜን ምስራቅ ኮንሶና በደቡብ ወንጮ አከባቢ ከባድ ዝናብ ተመዝግቧል።
በኮፈሌና ሻኪሶ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ሲጥል፥ በላንጋኖ ሀይቅ አከባቢ እና በደቡብ ምዕራብና በምዕራብ ያቤሎ እንዲሁም በደቡብ ጉግዳ ቀለል ያለ ዝናብ ጥሏል።
ደመናን የማበልፀግ ቴክኖሎጂ ደመናን ወደ ዝናብ ለመቀየር ከማስቻሉ በተጨማሪ ዝናብ በሚፈለግበት ቦታ እንዲዘንብ ያስችላል።
እንደ ባለሙያዎች ማብራሪያ ደመናን ለማበልፀግ በመጀመሪያ በከባቢ አየር ውስጥ ለመበልፀግ በቂ የሆነ ደመና መኖሩን ማረጋገጥን ይጠይቃል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!