Fana: At a Speed of Life!

በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ሆስፒታሎች 6 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሃዮ ስቴት ግሎባል ዋን ሄልዝ በአማራ እና አፋር ክልሎች ጉዳት የደረሰባቸው ሆስፒታሎቸን መልሶ ለማቋቋም የሚውል 6 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚያወጣ የላብራቶሪ ህክምና ቁሳቁስ ድጋፍን አድርጓል፡፡
 
ድጋፉን የተረከቡት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አየለ ተሾመ÷ የጤናው ዘርፍ በጦርነቱ ከፍተኛ ውድመት ያሰተናገደ መሆኑን ገልጸው÷የተደረገው ድጋፍ ያጋጠሙ ችግሮች ለመቅረፍ የሚረዳ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
 
የላብራቶሪ ህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ የተደረገላቸው ተቋማት የተሟላ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት እንዲችሉ እየተደረገ ያለውን ጥረት የሚያግዝ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
 
የኦሃዮ ስቴት ግሎባል ዋን ሄልዝ ቴክኒካል ዳይሬክተር ዶክተር ኤባ አባተ በበኩላቸው ÷ተቋማቸው ከጤና ሚኒስቴር እና ከተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ጋር ላለፉት 10 ዓመታት ሲሰራ መቆየቱን አውስተዋል፡፡
 
በ18 ሚሊየን ዶላር በጀት የ5 ዓመት ፕሮጀክት በመተግበር ላይ እንደሚገኝ እና ከሚሰራቸው ስራዎች በተጨማሪ በጦርነት ጉዳት ለደረሰባቸው የጤና ተቋማት የሚያደርገውን ስልጠና እና ድጋፉ አጠናክሮ እንደሚቀጥል መናገራቸውንም ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.