Fana: At a Speed of Life!

የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም የጸጥታ ችግር በነበረባቸው አካባቢዎች የተመዘገበውን የተማሪዎች ውጤት ዳግም ማየት የሚቻልበት ሁኔታ እንዲኖር ምክረ ሀሳብ አቀረበ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስቴር በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናን አስመልክቶ የጦርነት ወይም የጸጥታ ችግር በነበረባቸው አካባቢዎች የተመዘገበውን የተማሪዎች ውጤት ዳግም ማየት የሚችልበትን ሁኔታ እንዲያመቻች የኢትዮጵያ ሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ምክረ ሀሳብ አቀረበ።

የ2013 ዓ.ም የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተናን አስመልከቶ በቀረበ ቅሬታና የተካሄደ ምርመራን መሰረት በማድረግ ባወጣው መግለጫ፥ ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ ተማሪዎች እና ቤተሰቦቻቸው ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ቅሬታቸውን ለማቅረብ ቢመጡም ተገቢውን ምላሽ አለማግኘታቸውንና ለእንግልት እየተዳረጉ እንደሚገኙ ማረጋገጡን አመላክቷል፡፡

ሀገር አቀፍ የፈተናዎች ኤጀንሲ የፈተና እርማትን አስመልክቶ ከሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ከተፈታኝ ተማሪዎች እና ወላጆች የሚቀርቡ አቤቱታዎችን ተገቢውን ጊዜ ሰጥቶ ያለምንም ገደብ በአካል፣ ኦንላይን የአቤቱታ ማቅረቢያ ጨምሮ ሁሉንም አማራጮች ተጠቅሞ አቤቱታዎች በመቀበል ተገቢውን የሰው ሀይል በመመደብ ለቅሬታዎቹ ግልጽ እና ምክንያታዊ ምላሽ እንዲሰጥ ነው የጠየቀው።

ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና በተሰጠበት ወቅት በሀገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች በተለይም በአፋር፣ አማራ እና በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጦርነት እና የጸጥታ ችግሮች የነበሩ መሆኑ በመንግስት በይፋ እንደሚታወቅ ጠቅሷል።

በመሆኑም የትምህርት ሚኒስቴር በጦርነት ወይም የጸጥታ ችግር በነበረባቸው አካባቢዎች የተመዘገበውን የተማሪዎች ውጤት በአንጻራዊነት ሰላም በነበረባቸው አካባቢዎች ከተፈኑ ተማሪዎች ውጤት ጋር ያለውን ልዩነት ወይም ተቀራራቢነት በማየት እና በሚያገኘው ግኝት መሰረት የተማሪዎች ወደ መንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሚያስገባው መቁረጫ ውጤት ላይ የሚኖረውን ተጽዕኖ ዳግም ማየት የሚችልበት ሁኔታ እንዲመቻች ተቋሙ ምክረ ሀሳቡን አቅርቧል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.