Fana: At a Speed of Life!

በቻይና የተከሰከሰው ቦይንግ 737 አውሮፕላን የመረጃ ሳጥን መገኘቱ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) ከቀናት በፊት በቻይና የተከሰከሰው ቦይንግ 737 የመንገደኞች አውሮፕላን የመረጃ ጥቁር ሳጥን መገኘቱ ተገልጿል፡፡

የቻይና ምስራቃዊ አየር መንገድ ንብረት የሆነው ቦይንግ 737 አውሮፕላን በደቡብ ቻይና ጓንግዚ ዙዋንግ ግዛት መከስከሱ የሚታወስ ነው፡፡

በአደጋው 9 የበረራ ሰራተኞችን ጨምሮ 123 ተሳፋሪዎች መካከል በህይወት የተረፈ አለመኖሩ ተረጋግጧል፡፡

አውሮፕላኑ በተከሰከሰበት ቦታ ፍለጋዎች ተጠናክረው የቀጠሉ ሲሆን፥ የበረራ መረጃን መዝግቦ የሚይዘው ጥቁር ሳጥን መገኘቱን ይፋ አድርገዋል።

አውሮፕላኑ ከመነሳቱ በፊት የበረራ ደህንነት መስፈርቶችን አሟልቶ እንደነበር እና ሁሉም የበረራ አባላት በጥሩ ጤንነት ላይ ይገኙ እንደነበር የቻይና ምስራቃዊ አየር መንገድ ባለስልጣን መግለፁን ሲ ጅ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡

የመረጃ ሳጥኑ መገኘት ትክክለኛ የአደጋውን መንስኤ ለማወቅ እንደሚረዳ ይታመናል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.