Fana: At a Speed of Life!

በድሬዳዋ የብልፅግና ፓርቲ ህዝባዊ የውይይት መድረክ በመካሄድ ላይ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ̋”የፈተናዎች መብዛት ከብልፅግና ጉዟችን አያስቆመንም! በሚል መሪ ሃሳብ በድሬዳዋ ብልፅግና ፓርቲ የተዘጋጀ ድህረ ጉባኤ የህዝብ ውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

በመርሀ ግብሩ የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የትራንፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስን ጨምሮ በብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና በድሬዳዋ የአስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ ከንቲባ ከድር ጁሀር ተገኝተዋል፡፡

በተጨማሪም ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች፣ የብልፅግና ፓርቲ አመራሮችና አባላት እንዲሁም የአስተዳደሩ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል፡፡

የድሬዳዋ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር የተጀመረውን ሀገራዊ ለውጥ በማስትፋና በማፅናት የህዝባችንን ሁሉንተናዊ ደህንነትን ማረጋገጥ የብልፅግና ፓርቲ ቀዳሚ አጀንዳ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በመጀመሪያው ጉባኤ የተቀመጡ አቅጣጫዎችን መሠረት በማድረግ እንደ ድሬዳዋ ለህዝቡ ሁለንተናዊ ሠላም፣ ደህንነትና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በትኩረት እንደሚሠራበትም ጠቁመዋል፡፡

አሁን ላይ የከተማዋን ሠላምና ደህንነት ማረጋገጥ፣ የኑሮ ውድነት እና የዋጋ ግሽበትን መቀነስ፣ ሌብነትን አምርሮ መታገልን ፣ የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ እና የሃይማኖት መካረርን ማርገብ በሚሉ እና በህብረ ብሔራዊ አብሮ የመኖር እሴትን ማጎልበት በሚል ለውይይት በቀረብ ጽሁፍ ላይ ውይይት እየተደረገ ይገኛል፡ ፡

በተሾመ ኃይሉ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.