የኢትዮጵያ ብሔራዊ ስታዲየም ግንባታን በቅርብ ጊዜ ለማጠናቀቅ እንሰራለን – የቻይና ስቴት ኮንስትራክሽን ኢንላይት ኢንጅነሪንግ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይና ስቴት ኮንስትራክሽን ኢንላይት ኢንጅነሪንግ ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ ዋንግ ቹንቺንግ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ስታዲየምን በፍጥነት ለመጨረስ በሚያስችል ጉዳይ ላይ ከባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጀላ መርዳሳ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ዋና ስራ አስኪያጁ ዋንግ ቹንቺንግ “የኢትዮጵያ ብሔራዊ ስታዲየም ግንባታ የዘገየው በውጭ ምንዛሪ የሚከፈለን ክፍያ በመዘግየቱ በ2020 ከውጭ ሀገር ተገዝተው የሚገቡ የግንባታ ዕቃዎች በወቅቱ ባለመገዛታቸው እና በየጊዜው የሚታየው የዋጋ ንረት ምክንያት ነወ” ብለዋል፡፡
“ምንም እንኳ ኩባንያው ቢጎዳም ግንባታውን በቅርብ ጊዜ ለማጠናቀቅ እንሰራለን” ነው ያሉት፡፡
አቶ ቀጀላ መርዳሳ በበኩላቸው፥ ከውጭ ሀገር በዶላር ለሚገዙ የግንባታ ዕቃዎች የሚሆን 13 ነጥብ 5 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር መለቀቁን ጠቁመው፥ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል ክፍያው በቶሎ እንደሚፈፀምጠይቀዋል፡፡
፡፡
፡፡
ቀሪ ክፍያው እንደሚከፈልና ከግንባታው አማካሪዎች ጋር በመገናኘት በፍጥነት እንዲጠናቀቅ በሚያስችል ጉዳይ ላይ እንደሚወያዩ ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ያኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!