የከረዩ አባ ገዳዎችን ግድያ በተመለከተ በህጋዊና ባህላዊ መፍትሔ እልባት ለመስጠት እየተሰራ ነው – አቶ ሽመልስ አብዲሳ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የከረዩ አባ ገዳዎች ግድያን በተመለከተ ህጋዊ እና አባገዳዎች በሚያስቀምጡት ባህላዊ መፍትሔዎች እልባት ለመስጠት እየተሰራ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ተናገሩ፡፡
ድርጊቱ ትልቅ ስብራትን የፈጠረ እና በባህላችን ላይ የተቃጣ ድርጊት በመሆኑ ህጋዊ እርምጃው እንተጠበቀ ሆኖ በባህላዊ አካሄዶችም ችግሩን ለመፍታት ጥረት ይደረጋል ብለዋል።
ከአባ ገዳዎቹ ግድያ አንድ ቀን በፊት 40 በሚደርሱ የፀጥታ ኃይሎች እና ሌሎችም አመራሮች በተመሳሳይ ግድያ መፈፀሙን ጠቅሰው÷ በሁለቱም ቀናት በተፈፀሙ ድርጊቶች በመሳተፍ የተጠረጠሩትም በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አንስተዋል፡፡
ድርጊቱ የክልሉን ሕዝብ ባህልና ማንነት መንግስት የበለጠ ለማሳደግ ጥረት በሚያደርግበት ጊዜ የተፈፀመ መሆኑን ጠቁመው÷ በጉዳዩ ላይ አባገዳዎች አቅጣጫ እንዲያስቀምጡ እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በዚሁ መሰረት አባ ገዳዎቹ የሚጠቁሙትን ባህላዊ አካሄድ የክልሉ መንግስት ተቀብሎ በመተግበር ችግሩን ከመሠረቱ ለመፍታት ዝግጁ መሆኑንም አቶ ሽመልስ አብራርተዋል፡፡
በአፈወርቅ አለሙ፣ዳግማዊ ዴክሲሳ እና ገመችስ ታሪኩ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!