Fana: At a Speed of Life!

የዓለም የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት ቀን በዲቦራ ፋውንዴሽን ተከበረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም የአዕምሮ ዕድገት ውስንነት (ዳውን ሲንድረም) ቀን በዲቦራ ፋውንዴሽን አዘጋጅነት ለሁለተኛ ጊዜ በእግር ጉዞና በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል፡፡

ዕለቱ “አካታችነት መብት እንጂ ችሮታ አይደለም” በሚል መሪ ቃል ነው የተከበረ ነውየተከበረው፡፡

በዓለም ላይ ከሚወለዱ 1 ሺህ ህፃናት አንዱ ከአዕምሮ ዕድገት ውስንነት ጋር የሚወለድ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ ሲል ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

ይህን መሰል ዝግጅቶች ለዓመታት ተደብቀው የኖሩ ህፃናት እንዲወጡ፣ ማህበረሰቡም ስለ ጉዳዩ ያለውን ግንዛቤ እንዲያስተካክል እንደሚያግዝ በመርሃ ግብሩ ተመላክቷል፡፡

ይህን ችግር ለማቅለል እየሰሩ የሚገኙ ተቋማት እንዳሉ ሆነው ችግሩ ለአንድ ወገን የሚተው ባለመሆኑ መንግሥት ከፍተኛ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባም ተገልጿል።

በዝግጅቱ ላይ የዲቦራ ፋውንዴሽን መስራች አባዱላ ገመዳ እና የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰን ጨምሮ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ ከአዕምሮ ዕድገት ውስንነት ጋር የተወለዱ ልጆች እና ወላጆቻቸው በተገኙበት ነው የተከበረው፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.