Fana: At a Speed of Life!

በቤልግሪድ 2022 የቤት ውስጥ የዓለም ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለፍጻሜ አለፉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ1 ሺህ 500 ሜትር የቤልግሪድ 2022 የቤት ውስጥ የዓለም ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለፍጻሜ ማለፍ ችለዋል፡፡
 
በወንዶች የ1 ሺህ 500 ሜትር ማጣሪያ ታደሰ ለሚ 3 ደቂቃ ከ 38 ሰከንድ በመግባት ማጣሪያውን አንደኛ ሆኖ በማጠናቀቅ ለፍጻሜ አልፏል፡፡
 
በሌላኛው ምድብ የተሰለፈው ሳሙኤል ተፈራ ደግሞ 3 ደቂቃ ከ37 ሴኮንድ ውድድሩን አንደኛ ሆኖ በማጠናቀቅ ለነገ ምሽቱ ፍፃሜ ማለፍ ችሏል፡፡
 
የሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር የማጣሪያ ውድድር ደግሞ ከደቂቃዎች በኋላ እንደሚጀምር ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
 
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.