Fana: At a Speed of Life!

የክልሉ ካቢኔ በብልፅግና ፓርቲ ጉባኤ የተላለፉ አቅጣጫዎችን ወደ ተግባር መቀየር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ተወያየ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል መስተዳድር ካቢኔ በብልፅግና ፓርቲ አንደኛ ጉባኤ የተላለፉ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎችን ወደ ተግባር መቀየር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሂዷል፡፡
በውይይቱ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ እንደገለጹት÷ የዋጋ ግሽበትንና የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት በሀገር ደረጃ እየተከናወኑ ካሉ ተግባራት በተጨማሪ ከክልሉ ነባራዊ ሁኔታ አንፃርም ችግሩን ለማቃለል በትኩረት ይሰራል፡፡
በክልሉ በመሬት፣ በግዢና በገቢ አሰባሰብ ዘርፍ የሚስተዋሉ የሌብነት ችግሮች በአግባቡ ተመርምረው እርምጃ እንደሚወሰድ ጠቁመው÷ በተለይም የብድር፣ የማምረቻና የመሸጫ ቦታ ችግሮችን ለመቅረፍ እንዲሁም የክልሉን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ እንዲጎለብት እና በከተማ ፅዳትና ውበት ዘርፍ አመራሩ በትኩረት እንዲንቀሳቀስ አሳስበዋል፡፡
የፕሮጀክቶች አፈፃፀምን ለማሻሻል፣ በአገልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም የህዝቦችን አብሮ የመኖር እሴት ለማጎልበት አመራሩ በጊዜ የለኝ መንፈስ ሊሠራ እንደሚገባም ነው ርዕሰ መስተዳድሩ የተናገሩት፡፡
ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሚስራ አብደላ በበኩላቸው÷ በክልሉ የኢኮኖሚ አሻጥር የሚፈጥሩ አካላትን ከመከላከል በተጨማሪ ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ነው ብለዋል፡፡
የካቢኔ ዓባላቱም በመሆኑም በጉባኤው የተቀመጡ አቅጣጫዎችን እና የተላለፉ ውሳኔዎች ወደ ተግባር ለመቀየር በቁርጠኝት እንደሚንቀሳቀሱ አረጋግጠዋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.