Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ያጋጠመው የኃይል መቆራረጥ በሁለት ሣምንታት ውስጥ ይስተካከላል – የአዲስ አበባ ኤሌክትርክ አገልግሎት

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰሞኑን በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች ያጋጠመውን የኃይል መቆራረጥ ችግር በሁለት ሣምንታት ውስጥ ለማስተካከል እየተሠራ መሆኑን የአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡
ሰሞኑን በመዲናዋ የተለያዩ አካባቢዎች የተስተዋለው የኃይል መቆራረጥ በትራንስፎርመር መቃጠል ምክንያት የተፈጠረ መሆኑን የአዲስ አበባ ኤሌክትርክ አገልግሎት ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ገበየሁ ሊኪሳ ለፋና ብሮድካስትንግ ኮርፖሬት ገልጸዋል፡፡
በዚህም በሰበታ አንፎ በሚገኘው ማከፋፈያ ላይ ከሚገኙ ሦስት ትራንስፎርመሮች አንዱ በመቃጠሉና ከዚሁ ትራንስፎርመር ኃይል ያገኙ የነበሩ ዓለም ባንክ፣ ቤተል፣ ጦር ኃይሎች፣ ጀሞ እና ሌሎች አካባቢዎች ላይ የኃይል መቆረራጥ እና መጥፋት ተከስቷል ብለዋል፡፡
የተቃጠለውን ትራንስፎርመር በፍጥነት ገዝቶ መተካት ስላልተቻለ እና የራሱ የአሰራር ሂደት ስላለው አካባቢዎቹ ላይ ለቀናት ኃይል ተቋርጦ መቆየቱንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎትም ችግሩን በጊዜያዊነት ለመፍታት ቀሪዎቹ ሁለት ትራንስፎርመሮች ተጨማሪ ኃይል እንዲሸከሙ በማድረግ የተቋረጠውን የኃይል ስርጭት ለመቀጠል ጥረት ማድረጉን ጠቁመው÷ በዚህም በመዲናዋ ካሉ የኃይል ማከፋፈያዎች ኃይል በማበዳደር ሙሉ በሙሉ የተቋረጠባቸው አካባቢዎች በፈረቃ ኃይል እንዲያገኙ የማድረግ ስራ እየተከናወነ መሆኑን አብራርተዋል፡፡
ችግሩም በቀጣይ ሁለት ሳምንታት ሙሉ በሙሉ እንደሚፈታ ነው ሥራ አስፈጻሚው የተናገሩት፡፡
በትዕግስት አብርሃም
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.