Fana: At a Speed of Life!

ሚኒስቴሩ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምርጫቸውን እስከ መጋቢት 13 እንዲያስተካክሉ አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስቴር ወደ መንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የሚገቡ ተማሪዎች አስፈላጊ መረጃዎችን እስከተፈቀደው የጊዜ ገደብ ድረስ እንዲያሟሉ ጥሪ አቅርቧል፡፡

በ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው ባስመዘገቡት ውጤት መሠረት በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ምደባ ማግኘት የሚያስችሉ ተማሪዎች ከዚህ ቅደም የተቋም እና የመስክ ምርጫ ማካሄዳቸውን ሚኒስቴሩ አንስቷል፡፡

በቅርቡ ምደባ የሚያደርግ መሆኑን የጠቀሰው ሚኒስቴሩ ፥ስለሆነም ተማሪዎች የሚከተሉትን መረጃዎች እንዲመለከቱ ጠይቋል፡፡

ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲዎችን የቅበላ አቅም፣ የተማሪዎች አማካይ ውጤት አፈፃፀም፣ ወዘተ ከግንዛቤ በማስገባት የዩኒቨርሲቲ ምርጫቸውን እስከ መጋቢት 13 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ በ Portal.neaea.gov.et ገብተው እንዲያስተካክሉ አሳስቧል፡፡

ሚኒስቴሩ ከምደባ በኋላም የሚቀርብ ምንም ዓይነት የምደባ ለውጥ የማያስተናግድ መሆኑንም አመላክቷል፡፡

በጤና እና ልዩ ልዩ ጉዳዮች ምደባ በልዩ ሁኔታ እንዲታይላቸው የሚያመለክቱ ተማሪዎች መረጃቸውን እስከ መጋቢት 11 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ በ https://student.ethernet.edu.et/ በኩል እንዲልኩም ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ በአካል የሚቀርብ ምንም ዓይነት ማስረጃ የማይስተናገድ እንደሆነ መገለጹን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.