Fana: At a Speed of Life!

መንግስት ሌብነትን ለማጋለጥ እያሳየ ያለውን ቁርጠኝነት ወደ ተግባር ለመቀየር እንሰራለን- የፌደራል ስነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግስት ሌብነትና ብልሹ አሰራርን ለማጋለጥ እያሳየ ያለውን የፓለቲካ ቁርጠኝነት ወደ ተግባር ለመቀየር እንሰራለን ሲሉ የፌደራል ስነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽነር ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ ተናገሩ፡፡
 
ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ የነበራቸው ኮሚሽነሩ በሀገሪቱ ተቋማዊ የመሰለውን የተደራጀ ሌብነት እና ብልሹ አሰራር በማጋለጥ ከከፍተኛ ባለስልጣናት እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ ተጠያቂነት ለማስፈን እንሰራለን ብለዋል።
 
ኮሚሽኑ ነፃና ገለልተኛ እንዲሁም ጠንካራ ተቋም ለማድረግም አደረጃጀቱን እየፈተሸ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡
 
ተቋማዊ አቋሙን በማስተካከልም በመንግስት እየታየ ያለውን ቁርጠኝነት ለመጠቀም እንሰራለን ብለዋል ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ፡፡
 
የመረጃ ስርአትን ማሳደግ እና ከዴሞክራሲ ተቋማት ጋር በቅንጅት መስራትም ቀጣይ ስራ መሆኑን ተናግረዋል።
 
የሀብት ምዝገባ ሂደትም ወደ ዲጂታል መቀየሩ ተመላክቷል፡፡
 
በሀይለኢየሱስ መኮንን
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.