ኢትዮጵያ እና ቻይና ሁለተኛውን የጋራ የፖለቲካ ምክክር አካሄዱ
በውይይቱ ወቅት በሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የሚደረጉ ውይይቶችና ተደጋጋሚ ጉብኝቶች በሀገራቱ መካከል ጠንካራ የፖለቲካ መተማመን እንዲፈጠር እንደሚያግዝ ተነስቷል።
አምባሳደር ሬድዋን በዚህ ወቅት ቻይና በፀረ ኮቪድ ዘመቻ ለኢትዮጵያ እያደረገች ያለውን ድጋፍ አድንቀው፥ ኢትዮጵያ ከቻይና ኩባንያዎች ጋር በመሆን የኮቪድ-19 ክትባትን በሀገር ውስጥ የማምረት ፍላጎት እንዳላት ገልጸዋል።
የቻይናው ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በበኩላቸው÷ ቻይና ለኢትዮጵያ እያደረገች ያለውን የኮቪድ -19 ክትባት ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቅሰው፥ የኮቪድ-19 ክትባትን ከኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለማዘጋጀት የሚፈልጉ ኩባንያዎቿን እንደምታበረታታ አስረድተዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ