Fana: At a Speed of Life!

አዲስ የተመሰረተው የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ የመጀመሪያ ስብሰባውን አካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ የተመሰረተው የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ የመጀመሪያ ስብሰባውን ዛሬ አካሂዷል፡፡
በስሰባውም የፓርቲው ጉባዔ ያስተላለፋቸው ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች በሚተገበሩበት ሁኔታ ላይ መክሯል፡፡
ማዕከላዊ ኮሚቴው የጉባዔው ውሳኔዎች ተግባራዊ የሚሆኑበት እቅድ ተዘጋጅቶ ውሳኔዎቹና አቅጣጫዎቹ በፍጥነት መተግበር እንዲጀምሩ ውሳኔ ማስተላለፉን ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኮሚቴው በተጨማሪም አዲስ የተገነባውን የብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት የመረቀ ሲሆን÷ በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄዱ ያሉ ሌሎች የልማት ፕሮጀክቶችንም በመጎብኘት ላይ ይገኛል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.