Fana: At a Speed of Life!

የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት ሕንጻ ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ ባለ 9 ወለል የዋና ጽህፈት ቤት ሕንጻ የምረቃ መርሃ ግብር የፓርቲው ፕሬዚዳንት፣ ምክትል ፕሬዚዳንቶች እና የፓርቲው ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ተመረቀ፡፡

በመርሃግብሩ ንግግር ያደረጉት የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ዐቢይ አሕመድ÷ ያማረ ህንጻ መገንባት ብቻ ሳይሆን ያማረ አስተሳሰብን መፍጠር አስፈላጊ ነው ብለዋል።

ያማረ ሕንጻ ገንብቶ ያማረች ሀገርና ያማረ አስተሳሰብን መፍጠር ቀጣይ ስራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ በበኩላቸው÷ ከአባላቱ በተደረገ መዋጮ እና ከደጋፊዎቹ በተገኘ ድጋፍ የተገነባ መሆኑን አንስተዋል።

ለግንባታውም 895 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገ ሲሆን÷ በውስጡ መዝናኛ እና መሰብሰቢያ አዳራሽን ያካተተ ነው ተብሏል፡፡

በግንባታ ሂደቱም ከ3 ሺህ በላይ ሰራተኞች እንደተሳተፉበት እና በ4 ሺህ 700 ካሬ መሬት ላይ ያረፈ ሕንጻ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በይስማው አደራው

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.