Fana: At a Speed of Life!

መዲናዋ ያስተናገደቻቸው ልዩ ልዩ ዝግጅቶች በሰላም ተጠናቀዋል-የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ አበባ ከተማ ያስተናገደቻቸው ልዩ ልዩ ዝግጅቶች በሰላም መጠናቀቃቸውን የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል አስታወቀ፡፡
በአዲስ አበባ ከመጋቢት 2 እስከ 4 ቀን 2014 ዓ/ም የብልፅግና ፓርቲ የመጀመሪያ ጉባኤ እንዲሁም መጋቢት 3 ቀን 2014 ዓ/ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 4ኛው ፓትረያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የአስከሬን ሽኝት ሥነ ሥርዓት በመስቀል አደባባይ ተካሂዷል፡፡
መጋቢት 4 ቀን 2014 ዓ/ም በመንበረ ፀበኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል የፀሎት ፣ የሽኝትና የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው ተፈፅሟል፡፡
በተመሳሳይ መጋቢት 4 ቀን 2014 ዓ/ም ታለቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለ19ኛ ጊዜ ያዘጋጀው የ5 ኪሎ ሜትር የሴቶች ሩጫ ተካሂጿል፡፡
በአጠቃላይ ከመጋቢት 2 እስከ 4 ቀን 2014 ዓ/ም ከተማዋ ያስተናገደቻቸው ልዩ ልዩ ሁነቶች (ዝግጅቶች) በሰላም እና በስኬት እንዲጠናቀቁ ድጋፍ ላደረጉ እንዲሁም ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ለተወጡ መላው የፀጥታ አካላት የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይሉ ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.