ኢንጂነር ታከለ ኡማ ለዶክተር ዐቢይ አሕመድ እና ለአቶ ደመቀ መኮንን የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የማእድን ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ የብልጽግና ፓርቲ ፕሬዚዳንት እና ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው ለተመረጡት ዶክተር ዐቢይ አሕመድ እና አቶ ደመቀ መኮንን የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ።
ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት መሪነት ለህዝብ ጥቅም በመኖር ይገለፃል፤መሪነት የራስን ህይወት ትቶ ሁሉን ነገር ለሀገር በመስጠት ፍቺውን ያገኛል ነው ያሉት።
“ወንድሜና የፓርቲያችን ብልፅግና ፕሬዚዳንት ዶክተር ዐቢይ አሕመድ መሪነትም በተግባር የተገለጠ፤ በወጀብ መሀል በስክነት መራመድን ከፍ አድርጎ ያሳየ የመምራት ምሳሌ ነው ብለዋል።
በዛሬው እለትም ፓርቲያችን ብልፅግና ዶክተር ዐቢይ አሕመድን የፓርቲው ፕሬዚዳንት አድርጎ መርጧልም ነው ያሉት።
“ለወንድሜ ዶክተር ዐቢይ አሕመድ እንኳን ደስ አለዎት እያልኩ በእርሳቸው የአመራርነት ዘመን ብልፅግና ያሰበውን እንደሚያሳካ እምነቴ የፀና ነው ብለዋል።
በተመሳሳይ አቶ ደመቀ መኮንን እና አቶ አደም ፋራህን ፓርቲያችን ብልፅግና ምክትል ፕሬዚዳንት በማድረግ መምረጡን ጠቅሰው፥ ለሁለቱም ከፍተኛ አመራሮች መልካም የስራ ዘመን እመኛለው ነው ያሉት ሚኒስትሩ፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!