Fana: At a Speed of Life!

ከብጹዕነታቸው የሰላምና ይቅርታን መንገድ በመማር ለአብሮነትና አንድነት ተባብሮ መስራት ያስፈልጋል- ፓስተር ጻድቁ አብዶ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከብጹዕነታቸው የሰላምና ይቅርታን መንገድ በመማር ለአብሮነትና አንድነት ተባብሮ መስራት ያስፈልጋል ሲሉ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት ፕሬዚዳንት ፓስተር ጻድቁ አብዶ ገለጹ።
ፓስተር ጻድቁ አብዶ በመስቀል አደባባይ በተከሄደው የብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሪዎስ አስክሬን ሽኝት መርሃ ግብር ላይ ባስተላለፉት የሀዘን መልዕክት÷ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የጠብን ግድግዳ በማፍረስ ለአንድነትና መተሳሰብ ሲሉ ለፈጣሪያቸው ታምነው የእውነትን መንገድ ተከትለዋል ብለዋል።
ብፁዑ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አንድ እንዲሆን ጉልህ ሚና እንደነበራቸው ማውሳታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በከንቱ የሚፈሰውን ደም በማስቆም ከጥፋት መንገድ መመለስ ይገባልም ነው ያሉት ፓስተር ጻዲቁ።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.