Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና ጂቡቲ በፀጥታና ደህንነት፣ በትምህርትና ስልጠና ዙሪያ በትብብር ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 28 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ጂቡቲ በመከላከያ ዘርፍ በፀጥታ እና ደህንነት እንዲሁም በትምህርትና ስልጠና ዙሪያ በትብብር ለመስራት ተስማሙ።
ስምምነቱን የፈረሙት የኢፌዴሪ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ኢትዮጵያ እና ጂቡቲ ታሪካዊና የረጅም ጊዜ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን አውስተው ፣ በባህልና በቋንቋም የጋራ አንድነት ያላቸው ወንድማማች ህዝቦች ናቸው ብለዋል።
የሁለቱ ሀገራት ጥምር የመከላከያ ሰራዊት ኮሚቴ በስትራቴጂክና በቴክኒክ በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ መደረሱ ለቀጠናዊው ሰላምና ፀጥታ መረጋገጥ ትልቅ ፋይዳ አለው ነው ያሉት።
ኢትዮጵያ እና ጂቡቲ የተለያዩ ዓለም አቀፍና አህጉር አቀፍ ተቋማት መቀመጫ ናቸው ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ÷ ሀገራቱ በሰላም ማስከበር ተልዕኮ ያላቸውን ሚና አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አንስተዋል።
የጂቡቲ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀኔራል ዘካሪያ ሼክ ኢብራሒም በበኩላቸው ÷ቀደም ሲል የሁለቱ ሀገራት ፌዴራል ፖሊሶች በድንበር አካባቢ የተለያዩ ወንጀሎችን በጋራ ለመከላከል መፈራረማቸውን ገልፀዋል።
አሁን ላይ በመከላከያ ደረጃ በትብብር ለመስራት የተደረጉ ስምምነቶች ለሃገራቱ የሚጠቅም ወሳኝ ስምምነት መሆኑንም ጠቁመዋል።
ቀደም ሲል የጂቡቲ ወታደሮች በኢትዮጵያ የተለያዩ ወታደራዊ ስልጠናዎችን የወሰዱ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን÷ በቀጣይም የዕውቀት ሽግግሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መጠቆሙን ከመከላከያ ሰራዊት ፌስ ቡክ ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
9ኛው የኢትዮ- ጂቡቲ የመከላከያ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሞች ስብሰባ በአዲስ አበባ የመከላከያ ጠቅላይ መምሪያ ተካሂዷል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.