Fana: At a Speed of Life!

ከ30 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የኮንትሮባንድ እቃ ተያዘ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ30 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የኮንትሮባንድ እቃ መያዙን በኢትዮጵያ ጉሙሩክ ኮሚሽን የአዋሽ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

በጽህፈት ቤቱ የኮንትሮባንድ መከላከል ቡድን መሪ ኢንስፔክተር አለሙ ይመር እንደገለጹት÷ የኮንትሮባንድ እቃው የተያዘው ትላንት ከምሽቱ 5 ሰዓት ላይ ነው።

ህገ-ወጦች የኮንትሮባንድ እቃውን ከሽነሌ ዞን ሙሉ ወረዳ አጓጉዞ ወደ መሀል ሀገር ለማስገባት ከቦርደዴ ከተማ ወጣ ብለው በሚገኙ የተለያዩ ጫካዎች ውስጥ በመደበቅ አመቺ ጊዜ እየተጠባበቁ እንደነበር ተመላክቷል፡፡

የጉሙሩክ ሰራተኞች ከህብረተሰቡ በደረሳቸው ጥቆማ መሠረት በየደረጃው ከሚገኙ የጸጥታ መዋቅሮች ጋር በመሆን ለተከታታይ ዘጠኝ ቀናት የኮንትሮባንድ ዋነኛ መተላለፊያ መንገድን ቆርጦ በመዝጋትና ጠንካራ የመረጃ ልውውጥ በማድረግ እቃዎቹን ከተደበቁበት መያዛቸውን ገልጸዋል፡፡

በዘመቻው የፌደራል ፖሊስ ኮንትሮባንድ መከላከል ዲቪዥን፣ የኦሮሚያ ልዩ ሀይል እና የምእራብ ሀረርጌ ዞን ፖሊስ አባላት መሳተፋቸውን ጠቅሰዋል ።

በጋራ በተደረገ አሰሳና ዘመቻ ከተደበቁበት የተገኙት እቃዎች ለአዋሽ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ገቢ ተደርገዋል፡፡

ከተያዙት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከልም ልባሽ ጨርቆች፣ የአዋቂ ሸሚዞችና ጫማዎች፣ የተለያዩ ሲጋራዎች፣ መድሀኒቶች፣ የሺሻ እቃዎች ይኙበታል፡፡ እቃዎቹ ሳይያዙ ቢቀር ኖሮ በሀገር ኢኮኖሚና በህብረተሰቡ ጤና ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትሉ ይችሉ ነበር ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡

እንደ ኢንስፔክተር አለሙ ገለጻ÷ አዘዋዋሪዎቹንም ሆነ ተባባሪዎቻቸውን ለመያዝ የተደረገው ጥረት ለጊዜው ባይሳካም በየደረጃው ከሚገኙ የጸጥታ አካላት ጋር በጋራ ክትትል እየተደረገባቸው ነው።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.