Fana: At a Speed of Life!

ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ የአየር ጥበቃ ፖሊስ አባላት እና ቴክኒሻኖች የምረቃ ስነ ስርአት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር ሃይል ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ የአየር ጥበቃ ፖሊስ አባላቱን እና ቴክኒሻኖች አስመረቀ፡፡
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ÷በሕግ ማስከበር እና በኅብረ ብሔራዊ አንድነት ዘመቻ ወቅት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አባላት እውቅናና የሜዳሊያ ሽልማት ተበርክቷል።
የኢትዮጵያ አየር ሃይል አዛዥ ሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳ፥ ለእለቱ ተሿሚዎች፣ ተመራቂዎች እና ቤተሰቦች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ተቋሙ ወደፊት ከፍ ማለት ሲገባው ባለፉት 27 አመታት ቁልቁል እንዲሄድ ሲደረግ መቆየቱን ሁሉም የሚገነዘበው እውነታ መሆኑን ጠቁመው÷ ተቋሙ በቀጣይ አስተማማኝ አቅሙን ማስቀጠል እንዲችል ትልቅ ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
በዚህ እልህ አስጨራሽ የተቋሙ የሪፎርም ስራ ላይ እያለን አሸባሪው ቡድን ባደረሰው ክህደት ጀግኖች ለከፈሉት መስዋዕትነት የላቀ አፈጻጸም ላበረከቱ አባላት አድናቆት በመስጠት ለዚህ ጀግንነት የበቁ ጀግኖችንም የእውቅናና የሜዳሊያ ሽልማት ለመስጠት መርሃ ግብሩ ተዘጋጅቷል ተብሏል።
በዛሬው እለት የስልጠና ጊዜያቸውን አጠናቀው የተመረቁ አባላትም የተጣለባቸውን ሃላፊነት በተገቢው መንገድ መወጣት እንዳለባቸው ሌተናል ጀነራል ይልማ አሳስበው፥ ሃገርን በመጠበቅ ሃላፊነታቸውን ለተወጡ የአየር ሃይል አባላት ክብር ይገባል ብለዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የተመራቂ አባላት ቤተሰቦች እና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።
በይስማው አደራው
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.