የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ ተማሪዎቹን አሥመረቀ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ በተለያየ የህክምና ትምህርት መስክ ያሰለጠናቸውን 475 ተማሪዎቹን አሥመርቋል።
ከተመራቂዎቹ መካከል 140 ያህሉ ሴቶች ናቸው፡፡
ሆስፒታሉ የተመሠረተበት 75ኛ ዓመት ክብረ በአልም በዚሁ የታሰበ ሲሆን÷ የኮሌጁ ፕሮቮስት ዶክተር ወንድምገኝ ገዛኸኝ የዘንድሮውን ምርቃት ከምስረታው ቀን ጋር መገናኘቱ ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።
ምሩቃኑ ከእለቱ የክብር አንግዳ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ እጅ ዲግሪያቸውን ተቀብለዋል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።