በዩክሬን የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ወደ ፖላንድ አቋርጠው እንዲገቡ መፈቀዱ ተገለፀ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሁኑ ወቅት በዩክሬን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወደ ፖላንድ ድንበር አቋርጠው መግባት እንዲችሉ ከፖላንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመነጋገር እና በመጻጻፍ ማስፈቀድ መቻሉን በጀርመን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ገለፀ።
በመሆኑም በዩክሬን የሚኖሩ እና ወደ ድንበር ጉዞ በማድረግ ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች በተቻለ ፍጥነት ወደ ሀገሪቷ ግዛት እንዲገቡ እና ወደ ኢትዮጵያ እንዲጓዙ ኤምባሲው አሳስቧል፡፡
ዜጎች ችግር እንዳይገጥማቸው በቅርበት እየተከታተለ መሆኑንም ኤምባሲው በመረጃው አሳውቋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!