Fana: At a Speed of Life!

ትምህርት ሚኒስቴር እና ብሪትሽ ካዉንስል በከፍተኛ ትምህርት የሰላም ጉዳይ ላይ በጋራ ለመስራት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ትምህርት ሚኒስቴር እና ብሪትሽ ካዉንስል በከፍተኛ ትምህርት የሰላም ጉዳይ ላይ በጋራ ለመስራት የሚያሥችላቸዉን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡
ስምምነቱን የተፈራረሙት የትምህርት ሚኒስቴር ዴኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ እና በኢትዮጵያ የብሪቲሽ ካዉንስል ካንትሪ ዳይሬክተር አቶ ነጻነት ደሞዝ ናቸዉ፡፡
በስነስርዓቱ ላይ የፕሮጀክቱ የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና አስተባባሪ ዶክተር ሃላ ኑርን ጨምሮ የብሪትሽ ካዉንስል ምክትል ዳይሬክተር ሰላማዊት አለማየሁ፣ ከብሪትሽ ካዉንስል እንዲሁም የትምህርት ሚኒስቴር ኃላፊዎች እና ፕሮጀክቱ የሚተገበርባቸዉ የሀዋሳ፣ ጅማ እና ባህርዳር ዩኒቨርስቲዎች ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡
ፕሮጀክቱ በሁለቱ አገራት መካከል ያለዉን የረጅም ጊዜ አጋርነት ማጠናከር፣ ዩኒቨርሲቲዎች ግጭትን በመከላከል እና የሰላም ግንባታ ያላቸዉን ሚና ማጎልበት እና ስርዓተ ጾታንና ከባቢያዊ ሁኔታን መሰረት ያደረጉ ሰላምን የሚመለከቱ ምርምሮች መደገፍ ላይ ያተኮረ ነው።
ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ እንዳመላከተው÷ በሂደት አገራዊ፣ ቀጠናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ደረጃ በሰላም ጉዳይ በጋራ መስራትን መነሻ ያደረገ ትብብርን የማጠናከር ዓላማ አለዉ፡፡
ስምምነቱ የዩኒቨርሲቲ ለሰላም ትምህርትን በአካባቢያዊ ግጭት ወቅት መተግበር የተባለዉ ፕሮጀክት በአዉሮፓ ኅብረት እና ብሪትሽ ካዉንስል የገንዘብ ድጋፍ በብሪትሽ ካዉንስል በምስራቅ አፍሪካ ኢትዮጵያንና ሱዳንን ማዕከል አድርጎ ይተገበራል ተብሏል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.