ብሔራዊ ቡድኑ በአለም ዋንጫ ማጣሪያ ያሳየውን ብቃት በአፍሪካ ዋንጫ መድገም አልቻልም-ኤሳያስ ጅራ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ብሄራዊ ቡድኑ በአለም ዋንጫ ማጣሪያ ያሳየውን ብቃት በአፍሪካ ዋንጫ መድገም አልቻልም ሲሉ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኤሳስ ጅራ ተናገሩ፡፡
አስልጣኝ ውበቱ አባተ እና ረዳቶቻቸው በካሜሮን የአፍሪካ ዋንጫ የነበራቸውን ቆይታ አስመልክቶ የ16 ክለቦች አሰልጣኞች በተገኙበት በድሬዳዋ ውይይት ተደርጓል፡፡
በውይይቱ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጅራ እንደተናገሩት፥ ብሔራዊ ቡድኑ በአለም ዋንጫ ማጣሪያ ያሳየውን ብቃት በአፍሪካ ዋንጫ መድገም አልቻልም ብለዋል፡፡
የቡድኑ ድክመት ምክንያት ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ሊግ ደካማ መሆኑ ነው በሚል አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ቀደም ብለው የሰጡትን አስተያይት ፕሬዚዳንቱ ተችተዋል፡፡
የቡድኑ ድክመት የሊጉ ደካማ መሆን ሳይሆን የባለድርሻ አካላት ድክመት ነው ብለዋል፡፡
በካሜሮን የአፍሪካ ዋንጫ ካደረግነው ዝግጅት አንፃር ከቡድን ማለፍ አለመቻላችን እንደ ተቋም አስቆጭቶናል ብለዋል ፕሬዚዳንቱ፡፡
ምርጥ ተጫዋች በስልጠና እንጂ ከሰማይ ሊመጣ አይችልም ያሉት ፕሬዚዳንቱ፥ ባጣናቸው ውጤቶች ላይ መፀፀት ሳይሆን ያየናቸውን ክፍተቶች ለማረም መስራት ይኖርብናል ብለዋል፡፡