ከ1 ሚሊየን በላይ ዜጎች ከተረጂነት መላቀቃቸው ተገለፀ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በመንግስትና በእርዳታ ድርጅቶች ድጋፍ ሲደረግላቸው የነበሩ ከአንድ ሚሊየን በላይ ሰዎች ከተረጂነት መላቀቃቸው ተገለፀ።
ከተረጂነት የተላቀቁት ዜጎች ባለፉት ሁለት ዓመታት በአየር ንብረት አደጋ እና በፀጥታ ችግር ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለው የነበሩ መሆናቸው ተነግሯል።
የብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የሎጀስቲክ ኦፕሬሽን ስራዎች ዳይሬክተር አቶ ሀይዳስ ሃሰን፥ ባሳለፍነው በ2011 ዓ.ም ከነበሩት 8 ነጥብ 5 ሚሊየን ተረጂዎች ውስጥ ከ1 ሚሊየን በላይ ተረጂዎች መቀነሳቸውን ተናግረዋል።
ከተረጂነት የተላቀቁትም በክረምቱ መግቢያና መውጫ የጣለው ዝናብ ተመጣጣኝ በመሆኑ፣ በህዝብ ለህዝብ እርዳታ እና በቁጠባ ብድር መነሻ ወደ ስራ በመሰማራታቸው ነው ተብሏል።
ለቀሪዎቹ 7 ሚሊየን 37 ሺህ ተረጂዎችም መንግስት ድጋፍ ማድረጉን እንደሚቀጥል ተመላክቷል።
በታሪክ አዱኛ
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision