Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የኅብረቱን የመሪዎች ጉባኤ በተሳካ መልኩ ማከናወኗ ለዓለም ትልቅ መልዕክት የሚያስተላልፍ ነው-ሱዳናዊቷ የአል-አረቢያ ዘጋቢ

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ 35ኛውን የኅብረቱን የመሪዎች ጉባኤ በተሳካ መልኩ ማከናወኗ ለዓለም ትልቅ መልዕክት የሚያስተላልፍ መሆኑን ሱዳናዊቷ የአል-አረቢያ ሚዲያ ዘጋቢ ሩፋይዳ ያሲን ገለጸች።
የዘንድሮው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ እንዳይካሄድ የተለያዩ የማሰናከያ ጥረቶች ቢደረጉም በጠንካራ የዲፕሎማሲ ስራ ጉባኤው በተሳካ መልኩ ተከናውኗል።
ኢትዮጵያ እንግዶቿን በጥሩ መስተንግዶ ተቀብላ በቆይታቸው እንዲደሰቱ በማድረግ ጉባኤው ሲጠናቀቅም በክብር ሸኝታለች።
በመሆኑም ኢትዮጵያ 35ኛውን የኅብረቱን የመሪዎች ጉባኤ በተሳካ መልኩ ማከናወኗ ለዓለም ትልቅ መልዕክት የሚያስተላልፍ መሆኑን ለዘገባ አዲስ አበባ የተገኘችው ሱዳናዊቷ የአል-አረቢያ ሚዲያ ዘጋቢ ሩፋይዳ ያሲን ገልፃለች።
”በእርግጥ ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት ሳስብ በአንዳንድ ሚዲያዎች በሚራገበው የተጋነነ ዘገባ ፈርቼ ነበር” የምትለው ጋዜኛዋ÷አዲስ አበባ ስደርስ ፍፁም ሰላማዊ እንቅስቃሴ ተመልክቻለሁ ብላለች።
አዲስ አበባ አምራና ተውባ በጥሩ መስተንግዶ ተቀብላን አስደሳችና የተሳካ ቆይታ አድርገናል ነው ያለችው።
ኢትዮጵያ አስደናቂና ሰፊ የተፈጥሮ ሃብት ያላት አገር መሆኑኗን የጠቀሰችው ጋዜጠኛዋ÷ደጋግመው ለመምጣት የሚያስቧትና የሚመኟት አገር ስትል ገልፃለች።
የኢትዮጵያ ሰላም የአፍሪካ ሰላም በመሆኑ ለሰላም፣ ልማትና አብሮነት አፍሪካዊያን በጋራ መቆም አለብን ማለቷንም ኢዜአ ዘግቧል።
ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችም ሚዛናዊ ዘገባዎቸን በማቅረብ እውነትን ብቻ መሰረት አድርገው መዘገብ አለባቸው ስትል መልዕክቷን አስተላልፋለች።

 

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.