ሻምፒዮን መሆን ልዩ ትርጉም አለው፣በአፍሪካ ስኬታማ ቡድንን ማሸነፍ ደግሞ ሌላ ስሜት ይሰጣል -አሊዮ ሲሴ
አዲስ አበባ፣ጥር 29፣2014 (ኤፍ ቢሲ) የሴኔጋል ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ አሊዩ ሲሴ በተጫዋችነት ዘመኑ የናፈቀዉን አፍሪካ ዋንጫ በአሰልጣኝነት አጣጥሞታል፡፡
የቀድሞው የሴኔጋል ብሄራዊ ቡድን ተጫዋች አሊዮ ሲሴ በተጨዋችነት ዘመኑ በ23ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ከካሜሮን ጋር በነበረ የፍፃሜ ጨዋታ መለያ ምት መሳቱን ተከትሎ ቡድኑ ዋንጫዉን አጥቷል፡፡
ሲሴ ከፀፀት ስሜቱ ሳይወጣ 2019 በተካሄደዉ 32ኛው የግብፅ አፍሪካ ዋንጫ ሴኔጋልን በአሰልጣኝነት እየመራ ለፍፃሜ ደርሶ ዋንጫውን በአልጀሪያ ተነጥቋል።
በመድረኩ ተስፋ ያልቆረጠዉ የሴኔጋል አሰልጣኝ ሲሴ፥ የአፍሪካ ዋንጫ ምኞቱን ለማሳካት ረዥሙን መንገድ ተጉዞ በሴኔጋል የአግር ኳስ ታሪክ የመጀመሪያ የሆነውን የአፍሪካ ዋንጫ ከቡድኑ ጋር ማንሳት ችሏል፡፡
ፈርኦኖቹን ድል በማድረግ ቡድኑ ሻምፒዮን ከሆነ በኋላ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጠው አሊዮ ሲሴ÷ እኔ የአፍሪካ ሻምፒዮን ነኝ፣ ረጅም ፣ አስቸጋሪ፣ አንዳንዴም ውስብስብ መንገዶችን እኔ እና ቡድኔ ተጉዘናል፤ ነገር ግን ተስፋ ሳንቆርጥ ምኞታችንን አሳክተናል ብሏል፡፡
የካሜሩንን የአፍሪካ ዋንጫ ማሸነፍ ልዩ ትርጉም አለው፣ በአፍሪካ በጣም ስኬታማ ቡድንን ማሸነፍ ደግሞ ሌላ ስሜት ይሰጣል፣ለሰባት ዓመታት ያህል ጠንክረን ስንሠራ ቆይተና ድሉም ይገባናል፣ተጫዋቾቼ እንኳን ደስ አላቹ ብለዋል ሲሴ በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ።
ሴኔጋል ሻምፒዮን መሆኗን ተከትሎ ከአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌደሬሽን(ካፍ) የ 5 ሚሊዮን ዶላር ተሸላሚ ስትሆን ግብፅ ደግሞ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ በማጠናቀቋ የ 2ነጥብ 7 ሚሊዮን ዶላር ተሸላሚ ይሆናሉ፡፡
በሚኪያስ አየለ
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!