Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ምርጥ 10 የኢንቨስትመንት መዳራሻ ሀገራት አንዷ ሆና ተመረጠች

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ከአፍሪካ በ2022 ምርጥ 10 የኢንቨስትመንት መዳራሻ ሀገራት ውስጥ አንዷ ሆና ተመርጣለች፡፡
እምቅ የኢንቨስትመንት አቅም እና ዕድሎች ካላቸው እና በያዝነው ዓመት ለኢንቨስትመንት ተመራጭ ከሆኑ የአፍሪካ ሀገራት ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗን ዓለም አቀፉ የቢዝነስ የሚዲያ አውታር “ቢዝነስ ኢንሳይደር” ያወጣው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ናይጀሪያ፣ ግብጽ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ አልጀሪያ፣ ሞሮኮ፣ ኬኒያ፣ጋና፣ አንጎላ እና አይቬሪ ኮስት ምርጥ የኢንቨስትመንት መዳረሻ መሆናቸው ተመላክቷል፡፡
ኢትዮጵያ በቢዝነስ ኢንሳይደር ምርጥ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ሆና ልትመረጥ የቻለችው፥ በአበባ ወጪ ንግዷ በአፍሪካ 2ኛ ደረጃን የያዘች ላኪ ሀገር በመሆኗ እና በቡና አምራችነቷ እንዲሁ ላኪነቷ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅናን በማትረፏ ነው ተብሏል፡፡
በተጨማሪም በኢትዮጵያ ውስጥ መዋዕለ-ነዋያቸውን ለሚያፈሱ ባለሐብቶች ማበረታቻ መቅረቡ ሀገሪቷን ለኢንቨስትመንት ተመራጭ እንዳደረጋት ተገልጿል፡፡
ከፈረንጆቹ 2019 እስከ 2020 ያለው የኢትዮጵያ የምጣኔ ሐብት ዕድገትም 6 ነጥብ 1 በመቶ እንደደረሰና ምንም እንኳን ሀገሪቷ በጦርነት ውስጥ ብትሆንም ጠቅላላ የሀገር ውስጥ እድገት መጠን 93 ነጥብ 97 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር መድረሱን ዘገባው አመላክቷል፡፡
በፈረንጆቹ 2022 የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በ8 ነጥብ 7 በመቶ ዕድገት እንደሚያሳይ እና ይህም በሀገሪቷ መዋዕለ-ንዋያቸውን ለሚያፈሱ ባለሐብቶች መነሳሳትን የሚፈጥር በጎ ዜና ነው ብሎታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.