Fana: At a Speed of Life!

በዚህ ዓመት 400 የመንግስት አገልግሎቶች በኦንላይን ለመስጠት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2014 ዓ.ም 400 የመንግስት አገልግሎቶችን ኦንላይን ለመስጠት እየተሰራ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገለጸ።

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በለሙ መተግበሪያዎች ላይ የሚሰጡ 168 አገልግሎቶች በኦንላይን እየተሰጡ ይገኛሉ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ሁሪያ አሊ፥ የኦንላይን አገልግሎት ዜጎች በወረዳና ቀበሌ ጭምር ቅሬታ የሚያነሱባቸውን የመንግስት አገልግሎቶች በተቀላጠፈና ተጠያቂነት በተሞላበት መልኩ ለመስጠት ያስችላል ብለዋል።

የዜጎችን እንግልት ለመቀነስ እና ጊዜና ጉልበትን ለመቆጠብ የመንግስት አገልግሎቶችን ኦንላይን ለመስጠት እየተሰራ መሆኑን የተናገሩት ሚኒስትር ዴኤታዋ፥ በሚቀጥሉት አስር ዓመታት 2 ሺህ 500 የመንግስት አገልግሎቶችን በኦንላይን ለመስጠት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ሚኒስቴሩ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተመረጡ የመንግስት አገልግሎቶችን በኦንላይን ለመስጠት የሚያስችል ስልጠና ለሁሉም የክፍለ ከተማ ባለሙያዎች ሰጥቷል።

ስልጠናው ባለሙያዎቹ በኦንላይን የሚሰጡ የመንግስት አገልግሎቶች በሁሉም ክፍለ ከተሞች ሳይቆራረጡ ለዜጎች እንዲደርሱ ለማድረግ የሚያስችላቸው ነው።

ሰልጣኞቹ በአዲስ አበባ ከተማ የሚሰጡ የኦንላይን አገልግሎቶች ሳይቆራረጡ እንዲሰጡ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያደርጉም ነው የጠየቁት።

በዚህም በተያዘው 2014 ዓ.ም 400 የመንግስት አግልግሎቶችን ኦንላይን ለመስጠት እየተሰራ መሆኑን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.