Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከጅቡቲ፣ ዛምቢያ፣ ሶማሊያ፣ ሴራሊዮን ፕሬዚዳንቶች እንዲሁም ከመንግስታቱ ድርጅት ምክትል ፀሀፊ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከጅቡቲ፣ ዛምቢያና ሶማሊያ ፕሬዚዳንቶች እንዲሁም ከመንግስታቱ ድርጅት ምክትል ፀሀፊ ጋር መወያየታቸውን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ፡፡

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ 35ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባኤን አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸውም ፥ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጅቡቲ ጋር የቆየው ወዳጅነት ተጠናክሮ በሚቀጥልበት ጉዳዮች ዙሪያ እንዲሁም የኢትዮጵያ የወጪ ንግድ እየጨመረ በመምጣቱ ይህን ማሳለጥ ላይም ሃሳባቸውን ማጋረታቸውን ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፥ ጅቡቲ በአካባቢው ሰላም እንዲፈጠር እያደረገችው ያለውን ጥረት ማድነቃቸውም ነው የተነሳው።

የጅቡቲ ፕሬዚዳንት ኦማር ጊሌ ፥ ኢትዮጵያ ቤቴ ነች ሲሉም ነው የተናገሩት፡፡

በተመሳሳይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከዛምቢያ ፕሬዚደንት ሃካይንዴ ሂቺልማ ጋር ባደረጉት ቆይታ ፥ ሁለቱ ሃገራት በማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ መስኮች ትብብራቸውን ማጠናከር በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

ዛምቢያ በግብርናው መስክ ከኢትዮጵያ ልምድ መቅሰም እንደምትፈልግ ፕሬዚዳንቱ መናገራቸው በመግለጫው ተዳሷል።

ከመንግስታቱ ምክትል ዋና ጸሃፊ አሚና መሃመድ ጋር ዘላቂ ሰላምን ማስፈን እና ኢኮኖሚያዊ ድጋፍን ማጠናከር በሚቻልበት ዙሪያ መምከራቸውም ነው የተነሳው።

በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከሴራሊዮን ፕሬዚዳንት ጋርም ተወያይተዋል፡፡

ሴራሊዮን የኢትዮጵያን የበጋ መስኖ የስንዴ ልማት፥ አረንጓዴ ልማት ጋር አብሮ ለመስራት ፍላጎት እንዳላት ፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል።

በተጨማሪም ከሱማሌው ፕሬዚደንት መሃመድ አብዱላሂ መሃመድ (ፈርማጆ) ጋር የሁለቱን ሃገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ መምከራቸውን ሚኒስትሩ አንስተዋል።

በብስራት መለሰ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.