ግብፅ ካሜሩንን በመለያ ምት በማሸነፍ ለፍፃሜ አለፈች
አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ዋንጫው የፍጻሜ ጥሎ ማለፍ ጨዋታ በመለያ ምት ግብጽ ካሜሩንን 3ለ1 በማሸነፍ ከሴኔጋል በመቀጠል ለፍጻሜ ያለፈች ሁለተኛዋ ሀገር ሆናለች፡፡
ግብፅና ካሜሩን ለፍታሜ ጥሎ ማለፍ ባደረጉት ጨዋታ ከ90 ደቂቃው ባሻገር የጭማሪውን 30 ደቂቃ ያለግብ በማጠናቀቃቸው አሸናፊው በመለያ ምት እንዲለይ ተደርጓል፡፡
በዚህም ግብፅ በመለያ ምት ካሜሩንን 3 ለ1 በመርታቷ የፊታችን እሁድ ለዋንጫ ከሴኔጋል ጋር የምትጫዎት ይሆናል፡፡
የካሜሩን መለያ ምት መቺዎች 3 ኳሶችን በተከታታይ ማምከናቸው ለሽንፈት ዳርጓቸዋል፡፡
አዘጋጇ ካሜሩን የፊታችን ቅዳሜ ለደረጃ ከቡርኪናፋሶ ጋር የምትጫወት ይሆናል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!