Fana: At a Speed of Life!

አፍሪካ በሀገራት ብሔራዊ ጥቅም የሚዘወሩ የምዕራቡ ዓለም ተቋማት ያዛቡትን ምስሏን ለማስተካከል ጠንካራ አህጉራዊ የመገናኛ ብዙኀን ያስፈልጋታል- ምሁራን

አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አፍሪካ በሃያላን ሀገራት ብሔራዊ ጥቅም የሚዘወሩ የምዕራቡ ዓለም ተቋማት ያዛቡትን ገጽታዋን ለማስተካከል ጠንካራ አህጉራዊ የመገናኛ ብዙኀን ያስፈልጋታል ሲሉ ምሁራ ገለጹ፡፡

ምሁራኑ አህጉሪቱ ጠንካራ ሚዲያ የሌላት በመሆኑ የጨለማ፣ የጦርነትና የረሃብ ምድር ተደርጋ በውጭው አለም መገናኛ ብዙሃን እንደምትሳል አብራረተዋል፡፡

በዲላ ዩኒቨርስቲ የጋዜጠኝነትና ኮሚዩኒኬሽን መምህሩ አያሌው ደጀን ፥ አፍሪካ ጠንካራ አህጉራዊ ሚዲያ የሌላት በመሆኑ እውነቷ እንዲዛባ፥ ገጽታዋ እንዲጠለሽ ተደርጓል ይላሉ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባልደረባና የሚዲያ ባለሙያው ስላባት ማናዬ በበኩላቸው፥ የአሁኑን በአፍሪካ የምዕራባውያን ፍላጎት አስፈፃሚ መገናኛ ብዙሃንን መንገድ ለመመርመር በታሪክ ወደ ኋላ መመለስ ይገባል ነው የሚሉት፡፡

አዳዲስ አብዮቶች ከታዩባቸው ከ1980ዎቹ ወዲህ የቀድሞዎቹ የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ሬገንና የእንግሊዟ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርጋሬት ታቸር አክራሪ ገበያ መር (ኒዮ ሊበራሊዝምን) እንዲስፋፋ ያላቸውን ፍላጎት ሚዲያውም የነሱን ሀሳብና ርዕዮተ ዓለም እንዲይዝ ለማድረግ ሰርተዋል፡፡
ባለሙያዎቹ እነዚህ አካሄዶች የአፍሪካን እውነት የቀሙ ድምጧንም ያፈኑ ሆነዋል ነው ያሉት፡፡

የተደራጀ ደግሞም ተወዳዳሪ አፍሪካዊ ሚዲያ ያለመኖር የአፍሪካውያን ጉዳይ በሌሎች እንዲቃኝ፣ በሌሎች ተፅዕኖና ቅኝት ላይ እንዲወድቅም ምክንያት ሆኗል ሲሉ አክለዋል፡፡

ከጎርጎሮሳዊያኑ 2063 ወዲህ አህጉራዊ ሚዲያ ለማቋቋም እንቅስቃሴዎች መኖራቸውን በማንሳትም መንግስታት ይህንን ጅምር መደገፍና ማበረታት እንዳለባቸው ነው ያሳሰቡት፡፡

አህጉራዊ ጠንካራ ሚዲያ መፈጠሩ የአፍሪካን ድምፅ በማሰማት የመረጃ ፍሰቱን ሊያስተካክል እንደሚችልም ጠቁመዋል፡፡

በአፈወርቅ እያዩ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.