Fana: At a Speed of Life!

በተለያዩ የዓለም ሀገራት በተካሄዱ ውድድሮች ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አሸናፊ ሆነዋል

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሣምንቱ መጨረሻ በተለያዩ የዓለም ሀገራት በተካሄዱ የአትሌቲክስ ውድድሮች ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል፡፡
በጀርመን ካርልስሩህ የዓለም የቤት ውስጥ ቱር ውድድር በ3000 ሜትር በሪሁ አረጋዊ አንደኛ ደረጃን ሲይዝ÷ በሌላ በኩል ደግሞ በጣሊያን ቪቶሬ ኦሎና በተደረገ ቺንኩ ሙሉኒ አገር አቋራጭ ውድድር በወንዶች ንብረት መላክ አንደኛ፣ ታደሰ ወርቁ ሶስተኛ፣ ቢቂላ ታደሰ ደግሞ አራተኛ ሆነው ውድድሩን አጠናቀዋል፡፡
በስፔን ሲቪላ በተደረገ የግማሽ ማራቶን ውድድር በወንዶች ገብሬ እርቅይሁን ሶስተኛ ደረጃን ሲይዝ፥ በተመሳሳይ በስፔን ጌታፌ በተደረገ የግማሽ ማራቶን ውድድር በወንዶች ሀብታሙ ብርሌው ሁለተኛ ፣ስንታየሁ ድንቄሳ ደግሞ ሶስተኛ ደረጃ ወጥተዋል፡፡
በዚሁ መርሃ ግብር በሴቶች ቤተልሔም አፈንጉስ አንደኛ እንዲሁም ብርቱካን ወርቅነህ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቃቸውን ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.