Fana: At a Speed of Life!

አለም አቀፉ የፋይናንስ ተቋም በመንግስት ቅድሚያ የተሰጣቸው የኢንቨስትመንት ዘርፎችን ለመደገፍ ቁርጠኝነቱን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አለም አቀፉ የፋይናንስ ተቋም (አይ.ኤፍ.ሲ) ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ በመንግስት ቅድሚያ የተሰጣቸው የኢንቨስትመንት ዘርፎችን ለመደገፍ ያለውን ቁርጠኝነት ገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ሃላፊዎች ከተቋሙ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ቼክ ኦማር ሲላ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ዳይሬክተሩ፥ ተቋማቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ በመንግስት ቅድሚያ የተሰጣቸው የኢንቨስትመንት ዘርፎችን ለመደገፍ ያለውን ቁርጠኝነት በዚሁ ወቅት ገልፀዋል።

በተጨማሪም የሁለቱ ተቋማት ሃላፊዎች አሁን እየታየ ያለውን በኢንቨስትመንት ማስተዋወቅ፣ በንግዱ ከባቢ እና በተቋማዊ አቅም ግንባታ ዘርፎች የቅንጅት ስራ በጋራ አጠናክሮ ለመቀጠል ከስምምነት መድረሳቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.