በሽብር ቡድኑ የተጎዱ የምስራቅ አማራ አካባቢዎች የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶችን ወደ ስራ ለማስገባት ያለመ ውይይት እየተካሄደ ነው
በውይይቱ ላይ የደሴ ከተማ ከንቲባ አቶ አበበ ገብረመስቀል፥ በጦርነቱ ወቅት የነበረው መተባበር አሁን በመልሶ ግንባታው ላይ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ዶክተር ይልቃል ከፍአለ በበኩላቸው፥ ክልሉ የትኩረት አቅጣጫውን በተወሰኑ ዘርፎች ላይ በማድረግ እየተንቀሳቀሰ ነው ያሉ ሲሆን፥ በዋናነትም የፀጥታ ዘርፉን ማጠናከር እና በጦርነት ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸውን አካባቢዎች መልሶ መገንባት ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።
ኢንቨስትመንትን በማስፋፋትና የልማት ተግባራትን በማጠናከር ይሰራልም ብለዋል።
የውይይት መድረኩ ዋና አላማ በምስራቅ አማራ በጦርነቱ ምክንያት የወደመውን የኢንቨስትመንት ተግባር መመለስ መሆኑንም አንስተዋል።
በጋራ ተናበን በቅንጅት ከሰራን እንደምናሳካው አልጠራጠርም ነው ያሉት።
አዲስ መንፈስ፣ አዲስ የኢንቨስትመንት ስራ ለመፍጠር አሁኑኑ መነሳት አለብን ያሉት ርዕሰ መስተዳደሩ፥ ለዚህም መንግስት የድርሻውን ሀላፊነት ይወጣል ብለዋል።