ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በአፍሪካ ዊልቼር ቅርጫት ኳስ ውድድር ላይ የሚሳተፈውን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አበረታቱ
አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የአፍሪካ ዊልቼር ቅርጫት ኳስ ውድድር ላይ የሚሳተፈውን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አባላትን በአካል በመገኘት አበረታቱ።
ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በምታስተናግደው 11ኛው የአፍሪካ ዊልቼር ቅርጫት ኳስ ውድድር ላይ ብሔራዊ ቡድኗ በሁለቱም ፆታ ለማሳተፍ በዝግጅት ላይ ትገኛለች።
በወንዶች 6 በሴቶች 4 ሀገራት የሚሳተፉበት ይህ ውድድር በዱባይ ለሚዘጋጀው 14ኛው የአለም ዊልቼር ቅርጫት ኳስ ውድድር አፍሪካን የሚወክሉ ሀገራት የሚለይበት መድረክ ነው።
ዛሬ በአራት ኪሎ ወጣቶች እና ስፖርት ማእከል በሁለቱም ፆታ ለውድድሩ ዝግጅት ሲያደርጉ የነበሩትን የቡድኑ ተጫዋቾች ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች ተገኝተው አበረታተዋል።
ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ለውድድሩ ወደ ኢትዮጵያ ከሚመጡት 5ቱ የአፍሪካ ሀገራት ጋር ጥሩ ወንድማዊ ትስስር እንዲፈጥሩና በእንችላለን መንፈስ ውድድሩን ለማሸነፍ እንዲነሱ ተጫዋቾቹን ማሳሰባቸውን ኤ ኤም ኤን ዘግቧል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!