Fana: At a Speed of Life!

ቱርክ ገንዘቧ ከአሜሪካ ዶላር ጋር ያለውን ምጣኔ ለማስተካከል የፋይናንስ ማሻሻያዎችን አደረገች

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 1፣2014 (ኤፍ ቢሲ) ቱርክ ገንዘቧ ከአሜሪካ ዶላር ጋር ያለውን ምጣኔ ያስተካክላል ያለችውን የፋይናንስ ማሻሻያ ተግባራዊ ማድረግ ጀመረች።
ሰሞኑን የቱርክ ሊሬ ከአሜሪካ ዶላር አንፃር አቅሙ መዳከሙን ተከትሎ ፕሬዚዳንት ሬጂብ ታይብ ኦርዶኻን ይህን ችግር ይፈታል ያሉትን የፋይናንስ ማሻሻያ ይፋ አድርገዋል።
ፕሬዚዳንት ኤርዶኻን የሀገሪቱን መገበያያ ገንዘብ ሊሬ አቅም ያጠናክራሉ ያሏቸውን የፋይናንስ ማሻሻያዎችን ይፋ ማድረጋቸውን ተከትሎም በህዝቡ ዘንድ መረጋጋት መምጣቱ ተነግሯል።
ይህም የሊሬ ከአሜሪካ ዶላር አንፃር ያለው ምጣኔ የተወሰነ ጥንካሬ እንዲያሳይ እና የምንዛሪ ገበያው እንዲረጋጋ ማድረጉ ነው የተመለከተው።
የፕሬዚዳንቱን ንግግር ተከትየሊሬ ጤና በፍጥነት መመለስ ቀድሞውኑ በምንዛሪ ገበያው ላይ የተስተዋለው አለመረጋጋት ኢኮኖሚያዊ ምክንያት እንደሌለው ማሳያ ነው ተብሏል።
በዚህ በማሻሻያዎቹ መሰረት ዜጎች ገንዘባቸውን በሀገሪቱ ገንዘብ ሊሬ በባንክ እንዲያስቀምጡ የሚያበረታቱ ሲሆን፥ የዶላር አቅም በሚጠናከርበት ጊዜ ሊያጋጥማቸው የሚችለውን ኪሳራ መንግስት የግብር እፎይታ በመስጠት እና በሌሎች መንገዶች እንደሚሸፍን መጠቆሙን ሚድል ኢስት ሞኒተር ዘግቧል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.