Fana: At a Speed of Life!

በተለያዩ የዓረብ ሃገራት የሚኖሩ ሴቶች የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች ለመፍታት መንግስት መፍትሄ ያፈላልጋል – ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 7 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግስት በተለያዩ የዓረብ ሃገራት የሚኖሩ ሴቶች የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች ለመፍታት ከየሀገራቱ ጋር በመሥራት መፍትሄ እንደሚያፈላልግ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተለያዩ የዓረብ ሀገራት ከተውጣጡ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ጋር በአቡዳቢ ተወያይተዋል።

በውይይታቸው ዜጎች መደበኛ ባልሆነ ስደት ከሀገር ወጥተው ማረፊያቸው መጠለያ በመሆኑ፣ በደላሎች እና በቀጣሪዎች በደረሰባቸው በደል የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸዋል።

አያይዘውም መንግስት በተለያዩ የዓረብ ሃገራት የሚኖሩ ሴቶች የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች ለመፍታት ከየሀገራቱ ጋር በመሥራት መፍትሄ ያፈላልጋል ብለዋል።

በባህሬን የሚገኙ ዜጎችን ለማገዝም የቆንስላ ጽሕፈት ቤት እንደሚከፈት፣ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው እንዲኖራቸው ለማስቻል ውይይት እንደሚያደርጉም ተናግረዋል።

ከዚህ ባለፈም የመኖሪያ ፈቃድ ለማግኘት የሚያስችል ሁኔታ የሌላቸውን እና ለመመለስ የሚፈልጉትን መንግስት ወደ ሀገራቸው ይመልሳቸዋልም ነው ያሉት።

የውይይቱ ተሳታፊዎችም መደበኛ ባልሆነ መንገድ ከሀገር የሚወጡትን ለችግር የሚዳርጓቸው ደላሎች መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

ትክክለኛ መረጃ እና ማስረጃ በማቅረብ ከየሀገራቱ መንግሥታት ጋር በመሥራት የመፍትሄው አካል እንሆናለንም ብለዋል ተሳታፊዎቹ።

በውይይቱ ላይ በተለያዩ የስራ መስኮች ተሰማርተው እየሰሩ የሚገኙ ሴቶችን ጨምሮ በዓረብ ሀገር ቆይታቸው ስኬታማ የሆኑ ሴቶችም ተሳትፈዋል።

እንዲሁም ሰነድ አልባና እና በኤምባሲ ተጠልለው የሚገኙ ሴቶችም በውይይቱ ተገኝተዋል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.