Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያን ለማዳን አስፈላጊውን መስዋዕትነት እንከፍላለን – አምባሳደር ሄኖክ ተፈራ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 5 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያን ለማዳን አስፈላጊውን መስዋዕትነት እንከፍላለን ሲሉ በፈረንሳይ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሄኖክ ተፈራ ገለጹ፡፡

አምባሳደር ሄኖክ ተፈራ ከፈረንሳይ ሬዲዮ ጋር በተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ቆይታ አድርገዋል።

በቆይታቸው በትግራይ ክልል ተፈጽመዋል የተባሉ ውንጀላዎችን በተመለከተ የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እና ኢሰመኮ ያዘጋጁትን ሪፖርት ጨምሮ በርካታ ጉዳዮችን አንስተዋል።

በሁለቱ ድርጅቶች በጋራ ተጠንቶ የቀረበው ሪፖርት በኢትዮጵያ መንግስት ተቀባይነት ማግኘቱን ጠቅሰው፥ በአሸባሪው ህወሓት በኩል ሪፖርቱ እውነት ላይ የተመሰረተ እና አሸባሪ ቡድኑ በተደጋጋሚ ሲነዛቸው የነበሩ የሀሰት ውንጀላዎችን ያጋለጠ በመሆኑ ተቀባይነት ሳያገኝ መቅረቱን ገልጸዋል።

አሸባሪው ህወሓት መንግስት ርሃብን እንደ ጦር መሳሪያ ይጠቀማል በማለት በተደጋጋሚ ክስ ሲያቀርብ ቢቆይም በሪፖርቱ ውድቅ ተደርጎበታልም ነው ያሉት።

አያይዘውም በትግራይ ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ተፈጽሟል የሚለው ተደጋጋሚ ውንጀላም ሀሰተኛ መሆኑ ከመረጋገጡም በላይ በዚህ ግጭት የተፈፀመው የጅምላ ግድያ በህወሓት የተፈፀመ መሆኑን ሪፖርቱ አጉልቶ አሳይቷል ነው ያሉት።

በተለይም በማይካድራ ህወሓት የአንድ ብሄር አባል በመሆናቸው ብቻ በርካታ ንጹሃን ዜጎችን መጨፍጨፉን ሪፖርቱ ማጋለጡን አምባሳደር ሄኖክ አውስተዋል።

በሰብአዊ መብት ረገጣ የተጠረጠሩ በርካታ ወንጀለኞች ለፍርድ እንደቀረቡ መናገራቸውን ከዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.