አሜሪካ በሁዋዌ ላይ ተጨማሪ ክስ መሰረተች
አዲስ አበባ፣ የካቲት 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) አሜሪካ በቻይናው የቴክኖሎጂ ኩባንያ ሁዋዌ ላይ ተጨማሪ ክስ መመስረቷ ተገለፀ።
ዋሽንግተን ሁዋዌ ከአሜሪካ ኩባንያዎች ቴክኖሎጂዎችን ለመስረቅ የአስር ዓመት እቅድ ይዞ እየተንቀሳቀሰ ነው ስትል ተጨማሪ ክስ መስርታለች።
ጠበቃዎች ሁዋዌ ከአሜሪካ ኩባንያዎች ጋር የደረሰውን የትብብር ስምምነት በመጣስ የሮቦት ቴክኖሎጂ እና የተለያዩ ሚስጢራዊ መለያ ኮዶችን ሰርቋል ብለዋል።
ሆኖም ኩባንያው በአሜሪካ የቀረበበትን አዲስ ክስ አጣጥሏል።
ኩባንያው በዘርፉ የሚያካሂደው መስፋፋት የአሜሪካ ኩባንያዎችን ሊጎዳ ይችላል በሚል በአሜሪካ ኢላማ መደረጉ ነው የተገለፀው።
ከዚህ ጋር በተያያዘም በካናዳ የምትገኘው የኩባንያው መስራች ልጅ እና የፋይናንስ ሃላፊ ሜንግ ዋንዝሆው ለአሜሪካ ተላልፋ እንዳትሰጥ ስጋት አለ ተብሏል።
የፋይናንስ ሃላፊዋ በማጭበርበር እና በኩባንያው ላይ የተጣለውን ማዕቀብ በመተላለፍ በአሜሪካ ትፈለጋለች።
ምንጭ፦ ቢቢሲ