Fana: At a Speed of Life!

35ኛው የኅብረቱ ጉባኤ በሰላምና በስኬት ተጠናቆ መሪዎች ወደየሀገራቸው እየተመለሱ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 35ኛው የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ በሰላምና በስኬት በመጠናቀቁ የጉባኤው ተሳታፊ መሪዎች ወደ የሀገራቸው በመመለስ ላይ ናቸው፡፡

በዚህም መሰረት እስካሁን ባለው መረጃ  የኬንያ ፣የሞሪታኒያ፣የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ኮሞሮስ ፣ ጋና፣ ቤኒን፣ ዛምቢያ፤ ኮትዲቯር፥ ሊቢያ፣ ጅቡቲ፣ ሲሸልሽ ፣የማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ እና የኒጀር ፕሬዚዳንቶች እንዲሁም  የፍልስጤም ጠቅላይ ሚኒስትርን ጨምሮ የበርካታ ሀገራት መሪዎችና የልዑካን ቡድን አባላት ወደየሀገራቸው ተመልሰዋል።

 

 

ለሀገራቱ መሪዎቹና የልዑካን ቡድኖች ሚኒስትሮችና ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ቦሌ አለምአቀፍ አአውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው አሸኛኘት አድርገውላቸዋል።

በየሸዋ ማስረሻ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.