3ኛው የአፍሪካ ቢዝነስ ፎረም በአዲስ አበባ ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 3ኛው የአፍሪካ ቢዝነስ ፎረም በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ከተማ ተካሂዷል።
በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዘጋጅነት የሚካሄደው ፎረሙ “በህዝቦች፣ በፕላኔት እና በብልፅግና ላይ መዋዕለ ንዋይን” በሚል መሪ ቃል ነው የተካሄደው ።
የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ቬራ ሶንግዌ ፎረሙን በንግግር የከፈቱ ሲሆን፥ የተለያዩ ሀገራት መሪዎች እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች ተገኝተው ልምዳችውን አካፈለዋል።
የዚምባቡዌው ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ በፎረሙ ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት፥ ወደ ፊት ለመራመድ የኢነርጂ ዘፍር በጣም ወሳኝ ነው።
ዚምባቡዌ ላይ የተጣለው ማዕቀብ በሀገር ውስጥ የሚገኙ ሀብቶች ላይ ብቻ ጥገኛ እንድትሆን እንዳስገደዳትም ነው ፕሬዚዳንቱ ያነሱት።
በዛሬው እለት መካሄድ የተጀመረው መድረክ ላይ የአየር ንብረት ለውጥ በሚያስከትሉት ፈተናዎች፣ ቀጣይነት ያለው የኢነርጂ አቅርቦት፣ በጤና አጠባበቅ፣ በታዳሽ ሀይል፣ በመድሃኒት እና የህክምና ቁሳቁስ ማምረቻዎች፣ በአስተዳደር እና ቀጣይነት ያለው ልማት በሚሉ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን የሚያደርግ ነው።